አፍልቆት መር አቀራረብ የቃላት እውቀትን ለማሻሻል ያለው አስተዋጽኦ

  • Tamiru Geleta Student at AAU

Abstract

የዚህ ጥናት አቢይ አላማ አፍልቆት መር አቀራረብ አማርኛን እንደሁለተኛ ቋንቋ የሚማሩ የሰባተኛ ክፍል ተማሪዎችን የቃላት እውቀት ለማሳደግ ያለውን አስተዋጽኦ መፈተሽ ነበር። ይህን አላማ ለማሳካትም የአምቦ ሰደን ሊበን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትቤት በአመቺ ናሙና ተመርጧል። በትምህርትቤቱ ከሚገኙ አምስት ምድብ የሰባተኛ ክፍል ተማሪዎች የሁለት ምድብ ተማሪዎች በቀላል የእጣ ናሙና ተመርጠዋል። መረጃዎችም በቃላት እውቀት ፈተና በቅድመትምህርትና በድህረትምህርት ተሰብስበዋል። የተሰበሰቡት መረጃዎች በየአይነታቸው ከተደራጁ በኋላ ገላጭና ድምዳሜያዊ ስታትስቲክስ (ነጻ ናሙናዎች ቲ ቴስት) በመጠቀም ተተንትነዋል። በውጤት ትንተናው መሰረትም የሙከራው ቡድን ድህረትምህርት የቃላት እውቀት ፈተና አማካይ ውጤት ከቁጥጥር ቡድን የቃላት እውቀት ፈተና አማካይ ውጤት በልጦ ጉልህ ልዩነት ((t(182)=18.488, P<0.001)) አሳይቷል። ከዚህም በመነሳት አፍልቆት መር አቀራረብ የተማሪዎችን የቃላት እውቀት ለማሳደግ ከተለመደው የቃላት ማስተማርያ ዘዴ የበለጠ አስተዋጽኦ አለው ከሚል መደምደሚያ ላይ ተደርሷል። ይህን መደምደሚያ መሰረት በማድረግም ለአማርኛ ቋንቋ መምህራንና ተማሪዎች የአፍልቆት መር አቀራረብ አተገባበር በተመለከተ ስልጠና መስጠትና አቀራረቡን በስፋትና በአግባቡ መተግበር አስፈላጊ እንደሆነ አስተያየት ተሰንዝሯል። የወደፊት የጥናት ጥቆማዎችም ቀርበዋል።

ቁልፍ ቃላትና ሃረጋት፡- አፍልቆት፣ አፍልቆት መር አቀራረብ፣ የቃላት እውቀት

Downloads

Download data is not yet available.
Published
2026-06-23
How to Cite
Geleta, T. (2026). አፍልቆት መር አቀራረብ የቃላት እውቀትን ለማሻሻል ያለው አስተዋጽኦ. Journal of Culture and Language Studies , 2(2), 73-88. https://doi.org/10.59122/CJLS755
Section
Article