በአማርኛ ቋንቋ አንብቦ የመረዳት ችሎታ እና የማንበብ ግለብቃት እምነት ተዛምዶ፡ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተተኳሪነት

በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተተኳሪነት

  • Yidnekachew Geremew Alemu KUE

Abstract

በአማርኛ ቋንቋ አንብቦ የመረዳት ችሎታና የማንበብ ግለብቃት እምነት መካከል ያለውን ተዛምዶ መፈተሽ የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ ነው፡
፡ የተዛምዶ ፍተሻውን ለማድረግ ጥናቱ ተዛምዷዊ የምርምር ንድፍን ተከትሎ ተከናውኗል፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ አስተዳደር
በሁለት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ የአማርኛ ቋንቋ አፍፈት የሆኑ የ2013 የትምህርት ዘመን የአስራ አንደኛ ክፍል
ተማሪዎች ናቸው፡፡ የተሳታፊዎቹ አመራረጥ እኩል እድል ሰጭ ንሞና ዘዴ በመጠቀም ተከናውኗል፡፡ የአንብቦ መረዳት ችሎታ መለኪያ
ፈተናና የማንበብ ግለብቃት እምነት መጠይቅ በመጠቀም ለጥናቱ የሚያስፈልጉ መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ የተሰበሰቡት መረጃ
ከተጠናቀሩ በኋላ ገላጭ ስታትስቲክሳዊ ዘዴዎችን በመጠቀም ለጥናቱ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት የሚያስችል የመረጃ ትንተና
ተካሂዷል፡፡ ከመረጃ ትንተናው የተገኘው ውጤት (56.65%) የአብዛኞቹ ተማሪዎች አንብቦ የመረዳት ችሎታ መካከለኛ እንደሆነ
አሳይቷል፡፡ የተማሪዎቹ የማንበብ ግለብቃት እምነት አማካይ ውጤት (3.9) ከመካከለኛ በላይ መሆኑንም ከጥናቱ መረዳት ተችሏል፡፡
በተላውጦዎቹ መካከል ተዛምዶ መኖሩን ለመፈተሽ በተካሄደ የፒርሰን ተዛምዶ ትንተና መሰረት በአስራ አንደኛ ክፍል አማርኛ ቋንቋ
አፍፈት ተማሪዎች አንብቦ የመረዳት ችሎታ እና በማንበብ ግለብቃት እምነት መካከል አዎንታዊ ተዛምዶ መኖሩን የጥናቱ ውጤት
(r=.263) አሳይቷል፡፡ በጥናቱ ውጤት መነሻነት የተማሪዎችን የማንበብ ግለብቃት እምነት ማሳደግ የአንብቦ መረዳት ችሎታቸውን
ሊያዳብር ስለሚችል በመማር ማስተማር ሂደት ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አስተያየት ተሰጥቷል፡፡

Published
2021-12-01
Section
Articles