ይዘት ተኮር የቋንቋ ማስተማሪያ ዘዴ በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን አከራካሪ ድርሰት ከመጻፍ ክሂል አላባውያን ውስጥ ይዘትን እና የግለብቃት የመጻፍ ተነሳሽነት ላይ ያለው አስተዋፅዖ
Abstract
የጥናቱ ዋና ዓላማ ይዘት ተኮር የቋንቋ ማስተማሪያ ዘዴ በአከራካሪ ድርሰት ከመጻፍ ክሂል አለባውያን ውስጥ ይዘትን እና ከተነሳሽነት መገለጫ ከሆኑት ውስጥ የግለ ብቃት የመጻፍ ተነሳሽነትን ማጎልበት ላይ ያለው አስተዋፅዖንን መመርመር ነው፡፡ የጥናቱ ንድፍ ባለሁለት ቡድን ሙከራዊ ነው፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ መስተዳድር በዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም 10ኛ ክፍል ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ከነበሩ 609 /ስድስት መቶ ዘጠኝ/ ተማሪዎች መካከል በእድል ሰጪ ንሞና የተመረጡ የ10 ኛ - C ፣ የ10 ኛ- E እና የ10ኛ - H ክፍል ቡድኖችን ቅድመ የጽሁፍ ፈተና በመፈተን ተቀራራቢ ውጤት ያገኙትን የ10 ኛ - C እና የ10ኛ - E -ቡድኖች ለሙከራ እና ለቁጥጥር ቡድን ተሳታፊ እንዲሆኑ ተደርገዋል፡፡ ከእነሱም በፈተና፣ በጽሑፍ መጠይቅ እና በምልከታ አማካይነት የጥናቱ መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ በቅድመፈተና እና በቅድመ የጽሁፍ መጠይቅ የተገኙ ውጤቶች በነጻ ናሙና ቲ- ቴስት (Independent samples t-test) ተተንትነዋል፡፡ በትንተናው የተገኙት ውጤቶች እንደ ሚያመለክቱት በቅድመ ፈተና እና በቅድመ የጽሑፍ መጠይቅ ተመጣጣኝ አማካይ ውጤቶች የተመዘገበባቸው ቡድኖች፣ በድኅረፈተና በመጻፍ ክሂል ውስጥ ካሉት አላባውያን ውስጥ ይዘት እና በድኅረ የጽሑፍ መጠይቅ ደግሞ ግለብቃትን የሙከራ ቡድኑ ተማሪዎች ከቁጥጥር ቡድኑ ተማሪዎች ጉልህ የሆነ ልዩነት አሳይተዋል (P= <0.05)፡፡ ከዚህም በመነሳት ይዘት ተኮር የቋንቋ ማስተማሪያ ዘዴ የተማሪዎችን በአከራካሪ ድርሰት የመጻፍ ክሂል አላባውያን ውስጥ ይዘትእና ከመጻፍ ተነሳሽነት ግለብቃትን ለማጎልበት ከተለመደው የማስተማር ዘዴ የበለጠ ውጤታማነት አለው ከሚል መደምደሚያ ላይ ተደርሷል፡፡ በጥናቱ ውጤት መሰረትም ይዘት ተኮር የቋንቋ ማስተማሪያ ዘዴ የተማሪዎችን በአከራካሪ ድርሰት የመጻፍ ክሂል አለባውያን ውስጥ ይዘት እና ከመጻፍ ተነሳሽነት ግለብቃትን ለማጎልበት ያለው ውጤታማነት ጠቃሚ መሆኑ በመፍትሄነት ተጠቁሟል፡፡
ቁልፍ ቃላት፣ ይዘት፣ አደረጃጀት፣ ተነሳሽነት፣ ግለብቃት፣የመጻፍ ክሂል ችሎታ ድርሰት
Downloads
License and Copyright Agreement
EJBSS articles are distributed under the Creative Commons Attribution 4.0 License. Unless otherwise stated, associated published material is distributed under the same license.