በትምህርታዊ ጨዋታዎች የማንበብን ክሂል ማስተማር የተማሪዎችን የማንበብ ተነሳሽነት የማሳደግ ሚና ፍተሻ፤ አማርኛን እንደሁለተኛ ቋንቋ በሚማሩ የ5ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት

  • Wondimagegn Adem AAU

Abstract

የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ ትምህርታዊ ጨዋታዎችን ተጠቅሞ የማንበብ ክሂልን ማስተማር በተማሪዎች የማንበብ ተነሳሽነት ላይ ያለውን ሚና መመርመር ነው፡፡ ጥናቱ ፍትነት መሰል የምርምር ንድፍንየተጠቀመ ሲሆን አንድ የቁጥጥር ቡድን እና አንድ የሙከራ ቡድን የያዘ ነው፡፡ በእየቡድኑ 35 ተማሪዎች በጠቅላላ 70 ተማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡ አጥኚው የጥናቱን ቦታና ምድቦችን በአመቺ ንሞና ስልት፤ የክፍል ደረጃን(5 ክፍልን)እና መምህርመረጣን በዓላማ ተኮር ንሞና፤ የጥናቱ ተሳታፊዎችን ደግሞ በጠቅላይ የንሞና ስልት መርጧል፡፡ በመረጃ መሰብሰቢያነትም የቅድመ ትምህርትና የድህረ ትምህርት የማንበብ ተነሳሽነት ደረጃ መለኪያ የጽሁፍ መጠይቆችን ተጠቅሟል፡፡ ትምህርቱ 16 ሳምንታት የተሰጠ ሲሆንአጥኚው የሁለቱ ቡድን የማንበብ ተነሳሽነት ውጤቶችንተዛምዶ ለመለየት የፒርሰን የተዛምዶ መወሰኛ ቀመርን ተጠቅሟል፡፡ በተጨማሪም የነፃ ናሞና -ቴስት ስታትስቲካዊ መተንተኛ ስልትን በመጠቀም በእየቡድኖቹ የተገኘው የቅድመና ድህረ ትምህርት አማካይ፣ መደበኛ ልይይትና የጉልህነት መጠናቸው ተሰልተው ተተንትነዋል፡፡ውጤቱም የቅድመትምህርቱ የተዛምዶ መጠን (r= .067)እና የቁጥጥር ቡድኑ አማካይውጤት(M=51.29) የሙከራው(M= 50.54)ሲሆን፤የጉልህነት ደረጃውም(P= .581) በመሆኑ በሁለቱ ቡድኖች መካከል ጉልህ ልዩነት አለመኖሩን አሳይቷል፡፡ በአንፃሩ በድህረትምህርቱ የታየው የተዛምዶ መጠን(r= - .306) የድህረትምህርቱ አማካይ ውጤት የቁጥጥር ቡድኑ(M=51.77) የሙከራው(M= 55.06) ሆኖ ተገኝቷል፡፡ የጉልህነት መጠኑም (P= .010) በመሆኑ በሁለቱ ቡድኖች የማንበብ ተነሳሽነት ደረጃ መካከል ጉልህ ልዩነት መኖሩን አመላክቷል፡፡

ቁልፍ ቃላትና ሀረጋት : ትምህርታዊ ጨዋታ፣ የተለመደ የማስተማር ስልትና የማንበብ ተነሳሽነት

Downloads

Download data is not yet available.
Published
2024-07-28
How to Cite
Adem, W. (2024). በትምህርታዊ ጨዋታዎች የማንበብን ክሂል ማስተማር የተማሪዎችን የማንበብ ተነሳሽነት የማሳደግ ሚና ፍተሻ፤ አማርኛን እንደሁለተኛ ቋንቋ በሚማሩ የ5ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት. Ethiopian Journal of Business and Social Sciences, 6(2), 82-107. https://doi.org/10.59122/154F53lu
Section
Full Research Article