የጋሞ ዱቡሻ ዎጋ ሚና ግጭትን ከመከላከልና ዘላቂ ሰላም ከማፅናት አንጻር
Abstract
ሃገራችን ኢትዮጵያ የበርካታ ብዝሃ-ባህልና ብዝሃ-ልሳን ባለቤት ብቻ ሳትሆን የበርካታ ሀገርበቀል ዕሴቶች ባለቤትም ነች፡፡ እነዚህ ተቋማት ከጥንት ጀምሮ የህዝቦችን አንድነትንና ዘላቂ ሰላምን በማስፈን አይነተኛ ሚና እየተጫወቱ አሁን ድረስ ዘልቀዋል፡፡ ከነዚህ መሃከል የጋሞ ዱቡሻ አንዱ ሲሆን ይህ ጥናት የሚያተኩረው የጋሞ ዱቡሻ ዎጋ እንደ አገር በቀል ባህላዊ ተቋም ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ያለው ፋይዳ ይመረምራል፡፡ ዱቡሻ የጋሞ ማህበረሰብ ቀዳማይ(ባይራ) የእምነትና የባህል ተቋም ሲሆን ጥልቅ ፍልስፍናና ንጽረተ ዓለም የሚታይበት ዘርፈ ብዙ ፋይዳዎች ያሉት ሲሆን በብዛት የሚታወቀው ዘላቂ ሰላምን ከራሱ አልፎ ለሌሎች እንደጥሩ ምሳሌ ተደርጎ የሚወሰድ በመሆኑ ነው፡፡ በዚህ ጥናት ጥራት ተኮር የጥናት ዘዴ የተጠቀመን ሲሆን ከሁሉ የጋሞ ደሬዎች መረጃ የተሰበሰበው በቁልፍ ቃለ መጠየቅ፣ በአትኩሮት የቡድን ወይይትና ምልከታ በማድረግ በሂደቱም ከሃምሳ ሰዎች መረጃ ለመሰብሰብ ተችሎ ግኙቱንም ከሌሎች መረጃዎች ጋር ተከልስፏል፡፡ የጥናቱ ዉጤት እንደሚያሳው የጋሞ ማህበረሰብ ዱቡሻ ከጥንት ጀምሮ ችግራቸውን በመፍታት ሰላም ያስጠበቀ ዘመን ተሻጋሪ ሲሆን ህብረተሰቡም አሁን ደረስ ሳየበረዝና ሳይከለስ የጋሞን አንድነት በማጠንከር ለዘላቂ ሰላም ግንባታ የሚጫወተው በመሆኑ ለሌሎች ህዝቦች በተለይም ለአገራችን ዘላቂ ሰላምን ከመገንባት አኳያ ያለው ፋይዳው የጎላ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡ እንዲሁም ዱቡሻንና ሌሎች ተመሳሳይ የሀገርበቀል ተቋማትን ከዘመናውዊ ፍ/ቤት አሰራር ጋር በማቀናጀት መሰራት ቢቻል የህብረተሰቡን ጊዜና ገንዘብ ከመቆጠቡ ባሻገር ቁርሾን ከልብ በማውጥት የቀደመውን ማህበራዊ መስተጋብር በማደስ፤ ወቅታዊ ማህበረሰብ አቀፍ ቀውሶች በማስቀረት፣ ዘላቂ ሰላም እንዲኖር ዓይነተኛ ሚና ከመጫወት አልፎ አገር በቀል ባህላዊ ተቋማትና እሴቶች ለአገራዊ ሰላምና ብልጽግና ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ዱቡሻ እንደ ማሳያነት ቀርቧል፡፡
ቁልፍ ቃላት፡- ዱቡሻ ዎጋ፤ አገር በቀል ዕሴት፤ ጋሞ፤ ኢትዮጵያ
Downloads

This work is licensed under a Creative Commons Attribution-NonCommercial-NoDerivatives 4.0 International License.