አማርኛ ቋንቋ አፍፈት የሆኑ ተማሪዎችን የመጻፍ ችሎታ ለማሻሻል የፕሮጀክት ተኮር መማር ሚና ጾታ ተኮር ጥናት፤ በ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት

  • Simegn Alemneh Melie Woldia University

Abstract

የዚህ ጥናት ዓላማ አማርኛ ቋንቋ አፍፈት የሆኑ ተማሪዎችን የመጻፍ ችሎታ ለማሻሻል ፕሮጀክት ተኮር መማር ያለውን ሚ ከጾታ አንጻር መፈተሽ ነው፡፡ ዓላማውን ከግብ ለማድረስም መጠናዊ የምርምር ሂደትን የተከተለ ከፊል ፍትነታዊ (quasi-expermental) ስልት ተግባራዊ ሆኗል፡፡ በጥናቱ የትግበራ ሂደትም በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ማቻክል ወረዳ የሚገኘው አማኑኤል አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት በአመቺ ናሙና የተመረጠ ሲሆን በዚህ ትምህርት ቤት የሚገኙ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ደግሞ በዕጣ ናሙና ተመርጠው በጥናቱ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ ከተሳታፊ ተማሪዎች የተገኙት መረጃዎችም በባዕድ እና ጥንድ ናሙና ቲቴስት ተተንትነዋል፡፡ በተገኙት ውጤቶች መሠረትም፣ የሙከራ ቡድን ተማሪዎች የመጻፍ ችሎታ ውጤት ከቁጥጥር ቡድን ተማሪዎች የመጻፍ ችሎታ ውጤት ተሽለውና ጉልህ (p<.05) ልዩነት ያላቸው ሆነው ተገኝተዋል፡፡ እንዲሁም የሙከራ ቡድኑ ወንድ እና ሴት ተማሪዎች ተመጣጣኝ የመጻፍ ችሎታ ውጤትን (p>.05) አስመዝግበዋል፡፡ በዚህም መሠረት ፕሮጀክት ተኮር መማር የተማሪዎችን የመጻፍ ችሎታ ለማሻሻል ሚና እንዳለውና ሚናውም ለሴትም ሆነ ለወንድ ተማሪዎች እንደሆነ ጥናቱ አሳይቷል፡፡ ይህም የመጻፍ ትምህርትን በመማር ሂደትፕሮጀክት ተኮር መማር አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ አመላክቷል፡፡ በመሆኑም፣ የመጻፍ ትምህርትን በመማር ማስተማር ሂደት የፕሮጀክት ተኮር መማር ተግባራትን መጠቀም ለተማሪዎች ውጤታማነት አስተዋጽኦ እንዳለው ተጠቁሟል፡፡

Published
2021-06-01
Section
Articles