አዕምሯዊ የመማር ብልሐቶች የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት የማሻሻል ሚና፤ በሰባተኛ ክፍል ተተኳሪነት

Abstract

የጥናቱ ዓላማ አዕምሯዊ የመማር ብልሃቶች የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት የማሳደግ ሚና መፈተሽ
ነው፡፡ ዓላማውን ለማሳካት በ2011 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ በጊዮርጊስ ትምህርት ቤት በመማር ላይ የሚገኙ የሰባተኛ ክፍል
የአማርኛ ኢአፍፈት ተማሪዎች ሦስት መማሪያ ክፍሎች በአመቺ ንሞና ተመርጠዋል፡፡ ተሳታፊዎቹ በብልሃት 42፣ በብልሃትአልባ 38
እና በቁጥጥር 38 በድምሩ 118 ሲሆኑ፣ በአንብቦ መረዳት ፈተናና በማንበብ ተነሳሽነት የፅሁፍ መጠይቆች አማካይነት መረጃ
ሰጥተዋል፡፡ የተሰበሰበው መረጃ በገላጭና በድምዳሜያዊ ስታትስቲክስ (በባለሁለት ተላውጦ ልይይትና በባዕድ ናሙና ቲ-ቴስት
ተሰልቶ) ተተንትኗል፡፡ የጥናቱ ውጤቶችም በብልሃትና በብልሃትአልባ አቀራረቦች የተማሩት በተለመደው የማንበብ ትምህርት
ከተማሩት ይልቅ በአንብቦ መረዳት ችሎታቸው ጉልህ መሻሻል አሳይተዋል፡፡ ነገርግን በማንበብ ተነሳሽነት ላይ ጉልህ ሚና አላሳዩም፡፡
በብልሃትና በብልሃት አልባው ቡድን መካከልም የአንብቦ መረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት ጉልህ ልዩነት እንደሌለ ተረጋግጧል፡፡
ይህም ከሁለቱ የብልሃት አቀራረቦች አዕምሯዊ ብልሃትን በይዘትነትና በትግበራ መማርና በትግበራ ብቻ መማር ልዩነት እንደሌለው
ያሳያል፡፡ ስለዚህ ትግበራው በሁለቱም ቡድኖች ስለሚገኝ በይዘትነት ከመማር ይልቅ በትግበራ መማር አስተዋፅኦ እንዳለው
ያመለክታል፡፡

Author Biography

Hailay Tesfaye, Arba Minch University

Assistant Professor in Teaching Amharic (TeAm)

Published
2020-12-01
Section
Articles